የሙራድ ደንብ በአማርኛ / Murad Code in Amharic

በረቂቅ የሙራድ ደንብ ላይ በተካሄደው ዓለም አቀፍ ምክክር ወቅት የተገኘውን እጅግ ጠቃሚ እና ሰፊ ግብአት እና ምክረ ሃሳቦች  ተከትሎ  የተጠናከረ ግምገማ እና የማሻሻያ ሂደት ተደርጎ ተጠናቋል። ይህ የማሻሻያ ሂደት ተጎጂዎችን  እና ሌሎች ባለሙያዎችን በጽሁፍ ግምገማዎች እና በረቂቅ ማሻሻያዎች ላይ በተደረጉ ወርክሾፖች አሳትፏል። ይህም በሚያዚያ 5 ቀን 2014 ዓ.ም ይፋ የተደረገውን “ለስራ ሊውል” የሚችለውን አይነት የሙራድ ደንብ (“ስልታዊ እና ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃትን  የሚመለከት  መረጃን  መሰብሰብ እና መጠቀመን የሚመለከት ዓለም አቀፍ  የሥነ፟-ምግባር ደንብ”) ")  አስከትሏል፡፡

የሰኔ 2012 ዓመተ ምህረቱን ሪቂቅ የሙራድ ደንብ (በ እንግሊዘኛ፣ አረብኛ፣ ስዋሂሊ፣ ፈረንሳይኛ እና ስፓኒሽ የሚገኝ) ከግብረመልስ ማጠቃለያ ጋር (በእንግሊዘኛ ብቻ) እንዲሁም ከሰኔ 2012 ዓ.ም ጀምሮ የተገኙ ሙሉ የተሰባሰቡ ግብረመልሶች ጋር (በእንግሊዘኛ ብቻ) አሁንም ማግኘት ይቻላል፡፡  

የመጨረሻ ያልሆነ ነገር ግን በስራ ላይ ሊውል የሚችለው የሙራድ ደንብ የአማርኛ ቅጂ ከዚህ በታች ቀርቧል። ይህ ደንብ ስለስልታዊ እና ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃትን (SCRSV) በተመለከተ ደህንነቱ ለተጠበቀ፣ ውጤታማ እና ሥነ ምግባራዊ የሆነ የመረጃ አሰባሰብ መነሻ መስፈርቶችን ማንፀባረቅ መቀጠሉን ለማረጋገጥ በየጊዜው የሚገመገም ህያው ሰነድ ነው፡፡

የሙራድ ደንብ በሌሎች ቋንቋዎች የሚገኝ ሲሆን ከላይ ባለው ተቆልቋይ ሜኑ አማካኝነት ማግኘት ይቻላል።

ሙሉ ደንቡን በ አማርኛ ያውርዱ

PDF አውርድWord አውርድ